በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ትላንት በደረሰው ከፍተኛ ፍንዳታ የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እስካሁን ባለው መረጃ አንድ ወንድ ኢትዮጵያዊ በአደጋው ለሞት ሲዳረግ ሁለት ደግሞ መቁሰላቸው መረጋገጡን ለአል ዐይን ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ ያለው ቆንስላ ጽ/ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሆነ ያስታወቁት ቃል አቀባዩ በቀጣይ ጊዜያት ተጨማሪ መረጃዎች ሲደርሱ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡
በቤሩት በደረሰው ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ከ 100 መብለጡ የተገለጸ ሲሆን ተጎጂዎች ደግሞ 4ሺ ደርሰዋል ተብሏል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ