በኢትዮጵያ ተጨማሪ 583 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 26 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ከተመረመሩት 6907 ሰዎች መካከል 583 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን የ26 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በዛሬው እለት 330 ሰዎች ከኮሮና ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 7931 ደርሷል፡፡ በኢትዮጵያ እስካሁን 19289 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 444226 ሰዎች የኮሮና ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ