ወር የመጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ወላጆችን እያስገደዱ ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡
ይህንን ተከትሎም የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክተር ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ ማንኛውም ትምህርት ቤት ከነሀሴ ወር የመጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
ይህንን ወሳኔ አልፈው ምዝገባ በሚያካሂዱ ትምህርት ቤቶች ላይ አስፈላጊው የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ነው ወይዘሮ ሐረጓ የተናገሩት፡፡
የምዝገባው የግዜ ሰሌዳ እንዲራዘም የተፈለገው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ ወላጆች እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርጉትን ጉዞ በመግታት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ መሆኑን ዳይሬክተሯ አንስተዋል።
ወላጆችም መንግስት ትምህርት እንዲጀመር ሲያሳውቅ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አውቀው ልጆቻቸውን በእጃቸው ላይ የሚገኙትን የመማሪያ ቁሳቁሶች እንዲያጠኑ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ