ጁቬንቱስ የጣሊያን ሴሪ አን ለ9ኛ ተከታታይ ጊዜ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የቱሪኑ ክለብ ሴሪ አውን በተከታይ ለ9ኛ ጊዜ ማንሳቱን ትናንት ምሽት ሳምፕዶሪያን በማሸነፍ ነው ያረጋገጠው፡፡
ሁለት ጨዋታ በቀረው ሴሪ አ ጁቬንቱስ ከተከታዩ ኢንተር ሚላን የ7 ነጥቦች ልዩነት በመያዝ አሸናፊነቱን አውጇል፡፡
በምሽቱ ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ፌዴሪኮ በርናርዴስቺ የድል ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ጁቬንቱስ 36ኛ የሊግ ዋንጫውን ማሳካት ችሏል፡፡
የሊጉን 31ኛ ጎሉን ያስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአንድ የውድድር ዓመት 31 ጎል በማስቆጠር የክለቡን የቀድሞ አጥቂ ፌሊቼ ቦሬል ክብረ ወሰንን ተጋርቷል፡፡
ትናንት ምሽት በተካሄዱ የ36ኛ ሳምንት የሴሪ ጨዋታዎች ቦሎኛ ሊቼን 3 ለ 2 ሲያሸንፍ ካግሊያሪ በሜዳው በዩዲኒዜ 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ሮማ ፊዮሬንቲናን 2 ለ 1 እንዲሁም ላዚዮ ከሜዳው ውጪ ሄላስ ቬሮናን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ስታል ከቶሪኖ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ