Ads Here

ረቡዕ 5 ኦገስት 2020

በሚሊኒየም አዳራሽ የኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል የኦክሲጅን አልጋዎች ዕጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ።




በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከገባበት መጋቢት ወር አንስቶ ቫይረሱ ለተገኘባቸው ሰዎች ማከሚያ በሚል የተደራጀው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በመሙላቱ ነበር የሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ለይቶ ማከሚያነት የተደራጀው።

በዚህ የኮቪድ 19 ማገገሚያ ማዕከል የሚገቡ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በየጊዜው እያሻቀበ በመምጣቱ የጽኑ ህመምተኞች ቁጥር ጨምሯል።

እነዚህን ዜጎች በህይወት ለማቆየት ሲባልም የኦክስጂን አልጋዎች ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት እጥረት ማጋጠሙ ተገልጽል።

የሚሊኒየም COVID 19 ማገገሚያ ማአከል ዋና ዳሬክተር የሆኑት ዶ/ር ኤስማኤል ሸምሰዲን ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት ወደ ማገገሚያ ማእከሉ የሚገቡ የፅኑ ህሙማን ታካሚዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ  የኦክሲጂን አልጋዎችን እንዲጠቀሙ አስፈልጓል።

በመሆኑም ፅኑ ህሙማንን የሚያስተናግዱ የኦከሲጂን አልጋዎች በከፍተኛ ሁኔታ አስፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱን ነግረውናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ማእከሉ በአጠቃላይ 600 የሚሆኑ ታካሚዎች እያስተናገደ ቢሆንም  ከ 300 በላይ የሚሆኑት  የኦክስጅን ታካሚዎች መሆናቸውን  ነግረውናል፡፡

በአጠቃላይ በማእከሉ የሚገኘው የኦክስጂን አልጋ  380 ብቻ እንደሆነ የነገሩን ዶ/ር እስማኤል ይህም ቁጥሩ በየሰዓቱ እንደሚቀያየርና ነገር ግን አሁንም ቢሆን የኦክሲጅን አልጋዎች የሚያስፈልጋቸው  ታካሚዎች ቁጥር መጨመር  ሁኔታውን እጅግ ፈታኝ እንደሚያደርው ነግረውናል፡፡

ከዚህ ቀደም ማእከሉ ወደ ስራ ሲገባ በቀን ያስፈልግ የነበረው 10 ሲሊንደር ኦክስጂን በአሁኑ ሰዓት በቀን ወደ 100 ሲሊንደር ኦክስጂን ከፍ ማለቱም ለዚህ ማሳያ መሆኑን ነው የነገሩን ፡፡

በተለይም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ይህንን የፅኑ ህሙማን ቁጥር ማሻቀብ በዋናነት ህብረተሰቡ ያለው ቸልተኝነት  መሆኑን የሚናገሩት ዶ/ር አስማኤል በተለይም ወጣቶች ተያያዥ ህመም ያሉባቸውን ቤተሰቦቻቸውን ከልብ የሚወዱና  በህይወት እንዲቆዩላቸው የሚፈልጉ ከሆነ እንዲሁም በአጠቃላይ ለቤተሰቡ እና ለራሱ ህይወት የሚጨነቅ የሰው ፍጡር ሁሉ ይህንን ቫይረስ ለመከላከል ጥረት እንዲያደርግ ዶክተር እስማኤል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ