በሊባኖስ ቤሩት ባጋጠመው ፍንዳታ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ፡፡ፍንዳታው በከተማዋ ወደብ አቅራቢያ በሚገኙ መጋዘኖች አካባቢ ያጋጠመ ነው ያለው የሃገሪቱ የዜና አገልግሎት ከፍተኛ ጉዳት ማጋጠሙን ዘግቧል፡፡
እንደ ዜና አገልግሎቱ ከሆነ በስፍራው ነፍስ የማዳንና አደጋውን የመከላከል ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡
አንድ የአሶሼትድ ፕሬስ ፎቶግራፈር በፍንዳታው ምክንያት የተጎዱ ፍርስራሾችንና የመስተዋት ስባሪዎች በአካባቢው ተበታትነው ማየቱን ተናግሯል፡፡ በስብርባሪዎቹ የተጎዱ ሰዎችን በአካባቢው መመልከታቸውንም ነው የአይን እማኞች የገለጹት፡፡ ሆኖም ስለ አደጋው መንስዔ እና ስለ ጉዳቱ መጠን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም፡፡
ምስል፡ ከማህበረሰብ የትስስር ገጾች
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ