ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ባደረጉት ስብሰባ ኢትዮጵያ የበኩሏን የግድቡን ሙሌት ደንብ ማቅረቧን አስታወቀች፡፡ በቀረበው የሙሌት ደንብ ላይ ውይይት እንደሚደረግም የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሱዳንና ግብጽ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ደንብ ለመመልከት ጊዜ እንደሚፈልጉና እንድራዘምላቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም መሰረት ሀገራቱ የውስጥ ምክክራቸውን ሲያጠናቅቁ ድርድሩን ለመጀመር ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል፡፡
ቀጣዩ ስብሰባም የግብጽ ልዑክ ባቀረበው ሃሳብ መሰረት ነሀሴ 4 ቀን 2012 እንደሚቀጥል መግባባት ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡ኢትዮጵያ ያቀረበችው የግድብ ሙሌት ደንብ ምን ይዘት እንዳለው ሚኒስቴሩ ያለው ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር አንዳስታወቀው ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በአፍሪካ ህብረት መሪነት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያደርጉትን ድርድር በትናንትናው እለት ጀምረዋል፡፡ በህብረቱ ሲመራ የነበረው ድርድር መግባባት ላይ ሳይደረስ ነበር ከሁለት ሳምንታት በፊት የተቋረጠው፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ