በድንበር አቅራቢያ ሲበር የነበረ የኬንያ ጦር ሄሊኮፕተር ዶብሌይ ከተባለው የሶማሊያ አካባቢ የመከስከስ አደጋ እንደገጠመው ጎብጆግ የተሰኘው የሶማሊያ የዜና ተቋም አስነበበ፡፡
በአደጋው ያጋጠመ የሞት አደጋ የለም ያለው ጎብጆግ አብራሪውን ጨምሮ በ7 የበረራው አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘግቧል፡፡
ሄሊኮፕተሩ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር (አሚሶም) ስር ሆነው በታችኛውና በመካከለኛው ጁባ ሴክተር 2 እና 6 ለተሰማሩ የኬንያ ወታደሮች የድጋፍ ቁሳቁሶችን ሲያደርስ እንደነበር ዜናው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ሆኖም አደጋው ሄሊኮፕተሩ ለማረፍ በሚሞክርበት ወቅት ያጋጠመ ይሁን አይሁን አልታወቀም፡፡
እስካሁንም መቀመጫውን ሞቃዲሾ ካደረገው የአሚሶም መስሪያ ቤትም ሆነ ከኬንያ አየር ኃይል አደጋውን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ የለም፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ