Ads Here

ሐሙስ 6 ኦገስት 2020

በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አጅማን ከተማ የእሳት አደጋ ተከሰተ!

ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አንዷ በሆነችው አጅማን ፣ ትናንት ከአንድ ሱቅ እንደተነሳ የታመነው እሳት ቀስ በቀስ ሰፊ ቦታን ሸፍኖ ጉዳት አድርሷል፡፡ ቃጠሎው የተነሳበት ሱቅ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ለጥንቃቄ በሚል ለወራት ተዘግቶ የቆየ ነበር ተብሏል፡፡

የእሳት አደጋው የደረሰው በከተማዋ የኢንዱስትሪ ቀጣና አካባቢ ሲሆን በአቅራቢያው ከሚገኝ ሆስፒታል ሰራተኞች እና ታካሚዎች ለደህንነታቸው ሲባል በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እንዲወጡ ተደርጓል፡፡

የእሳት አደጋው በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ያደረሰው የጉዳት መጠን በዝርዝር አልታወቀም ሲል የሀገሪቱ ሚዲያ ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡ 

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ