Ads Here

ሐሙስ 6 ኦገስት 2020

የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመጥለፍ የተከሰሱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

 

የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመጥለፍ የተከሰሱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በእነ ከሊፋ አብዱረህማን የክስ መዝገብ የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ህዳር 24 እና 25/2012 ዓ.ም በመጥለፍ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት 17 ግለሰቦች መካከል ዘጠኙ በዛሬው ዕለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

በሦስት የሽብር ወንጀል የተከሰሱት ተከሳሾቹ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የተከሰሱበት ወንጀል ተነቦላቸዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ተከሳሾቹ በበኩላቸው ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቃወሚያ በጽሁፍ አቅርበዋል።

ከሳሽ ዐቃቤ ህግ በመቃወሚያው ላይ ምላሽ እንዲሰጥና ትእዛዝ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለነሐሴ 25/2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

1 አስተያየት: