በሊባኖስ መዲና በሆነችው ቤይሩት ውስጥ በተፈጠረው ከፍተኛ ፍንዳታ 10 ኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት መድረሱ እንደተረጋገጠ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ 10 ኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉ ታውቋል።
ከአደጋው በኋላ በስፍራው የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያዊያኑ ድጋፍ ማግኘት አለማግኘታቸውን የክትትል ስራ እየሰሩ መሆኑን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።
መንግስት ለዜጎቹ አስፈላጊውን ሁሉ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ