የሊባኖስ የህይወት አድን ቡድን የ135 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ፍንዳታን ተከትሎ የጠፉ ሰዎችን በመፈለግ ላይ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ዲያብ የሶስት ቀን ብሄሪዊ የሀዘን ቀን ያወጁ ሲሆን፤ እስካሁን በተደረገው ምርመራ ፍንዳታው የተከሰተው በቸልተኝነት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በፍንዳታው ህይወታቸውን ካጡት ሰዎች በተጨማሪ 5000 የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ከሩብ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በፍምዳታው ምክንያት ተፈናቅለው ቤት አልባ ሆነዋል፤ ፍንዳታው ባደረሰው መንቀጥቀጥ ምክንያት የህንጻዎችን የፊት ገጽ፣ የቤት እቃዎችንና የቤት መስተዋቶች ተሰባብረዋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ