ትናንት ቤሩትን ባናወጠው ፍንዳታ ከአንድ መቶ የሚልቁ ሰዎች መሞታቸው መሞታቸው መረጋገጡን የሃገሪቱ የዜና አገልግሎት ዘገበ፡፡
ፍንዳታው በአካባቢውና በቅርብ ርቀት ስፍራዎች ጭምር ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ማድረሱን ለዜና አገልግሎቱ የገለጹት የሃገሪቱ ቀይ መስቀል ኃላፊ ከ4 ሺ በላይ ሰዎችን ለጉዳት ስለመዳረጉም ለሃገሪቱ የዜና አገልግሎት ተናግረዋል፡፡
የአደጋው ሰላባዎች ገና በመፈለግ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ የሟቾቹና የተጎጂዎቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር ይችላል፡፡ ቤሩትን ያራደው ፍንዳታ 3 ነጥብ 3 ሬክተር ስኬል ልኬት ያለውን የመሬት መንቀጥቀጥ ያህል አካባቢውን እንዳንቀረቀበው መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ በከተማዋ ወደብ በሚገኝ አንድ መጋዘን ተከማችቶ በነበረ ከ2 ሺ 750 ቶን በላይ የምርት መጠን ማሳደጊያ ግብዓት (የአሞኒዬም ናይትሬት ኬሚካል ማዳበሪያ) ምክንያት የከፋ የተባለው ፍንዳታ ማጋጠሙንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዲያብ ተናግረዋል፡፡ ሊባኖስ በከፍተኛ ምጣኔ ሃብታዊ ድቀት ውስጥ እንዳለች የዘገቡ ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናዎች አደጋውን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ብለዋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ