በትላንትናው እለት በዋስ እንዲለቀቁ ከተባለ ብኃላ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት "የፖሊስን አቤቱታ የሚያይ ዳኛ ስላልተገኘ ሂሩት ክፍሌ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ያስጠበቀላቸውን መብት ፖሊስ ጥሶ በእስር እንዲቆዩ አድርጓል" ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ/ አስታውቆ ነበር ።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
የፖሊስን የይግባኝ አቤቱታ የሰማው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ትላንት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት ሂሩት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ፖሊስ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝን ሳይፈጸም ተጠርጣሪዎችን በእስር አቆይቶ ይግባኝ መጠየቁ ወንጀል ነው ሲል ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ #ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ