Ads Here

ረቡዕ 5 ኦገስት 2020

በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ 32 ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ



በአፋር ክልል ክረምቱን ተከትሎ እየጣለ ባለው ዝናብ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በ6 ወረዳዎች 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን በፅህፈት ቤቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲን ገልፀዋል ። ዳይሬክተሩ እንዳሉት በክልሉ በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ የሚገኙ 7 ወረዳዎች ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት ተጋላጭ ናቸው ።

ይህን ችግር ለመቅረፍ የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልሉ መንግስት አካላት ጋር በመቀናጀት የጎርፍ መከላከል ስራዎች ሲያከናውን ቢቆይም የዘንድሮው ክረምት ጠንከር ያለ በመሆኑ በ6 ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ ማጋጠሙን ዘግቧል።

ጎርፉን ተከትሎ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ግምቱ በመጣራት ላይ የሚገኝ ሰብልና እንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል ። በመሆኑም ከሰላም ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው የፌዴራል አካላት ጋር በመተባባር ከዛሬ ጀምሮ በሄሊ በውሃ የተከበቡት ሰዎች በሔሊኮፕተርና በሞተር ጀልባ በማውጣት ወደ ሌላ አካባቢዎች ለማስፈር የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም ከዳይሬክተሩ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል ።

በአፋር ክልል በታችኛውና መካከለኛው አዋሽ 63 ሺህ ሰዎች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ሲሆኑ 44 ሺህ ሰዎች በመፈናቀል ስጋት ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ