የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ላከናወኗቸው ውጤታማ ስራዎች የዕውቅና ሽልማት አበርክቷል።
ምክር ቤቱ ኢንጂነር ታከለየዕውቅና ሽልማቱ ያበረከተላቸው ÷ የሚሰሩ ስራዎች የከተማዋ ነዋሪዎችን ያማከለ እንዲሆን በማድረግ በኩል ውጤታማ ስራዎችን በማከናወናቸው ፣አስታዋሽ አጥተው ለዘመናት የተዘነጉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን በመስራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም የከተማዋን ታሪካዊና የቱሪዝም መስህብነት የሚያጎሉ እንዲሁም የነዋሪዎችን ችግር የሚፈቱና ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸው ታላላቅ ፕሮጀክችን ማስጀመራቸው በታሰበላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቅ በማስቻላቸው መሆኑም ተመላክቷል።
ከዚያም ባለፈ በከተማዋ ለሚገኙ ተማሪዎች ምግብ፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና ዩኒፎርም እንዲቀርብ አመራር መስጠታቸው ስራውንም ተቋማዊ እንዲሆን ማድረጋቸው ለሽልማቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል።
በኢኮኖሚው ዘርፍም የከተማ ግብርና በስፋት በከተማዋ ባህል እንዲሆን ሀሳብ በማመንጨትና አመራር በመስጠት እንዲሁም የእደጥበብ ዘርፎች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው እንዲጨምር እየሰሩ ያሉት ስራ ስኬታማ መሆናቸው ተነስቷል።
በአጠቃላይም ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከመሀል ከተማ ነዋሪ ጀምሮ አዋሳኝ ቦታ ላይ የሚገኙ አርሶ አደሮች ድረስ የባለቤትነት ስሜት በመፍጠር፣ የከተማዋ እድገት ሁሉንም ያካተተ እንዲሆን በማድረግ በኩል ባለፋት ሁለት ዓመታት ላደረጉት ስኬታማ ስራ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የእውቅና ሽልማት ማበርከቱን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ