ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ( ባይቶና)የወጣው መግለጫ የሚከተለውን ይመስላል
ባይቶና ፓርቲ የአማራ ክልል የመሬት ወረራ አዋጅና የፌዴሬሽን ምክርቤት የትግራይ የራስ እድል በራስ የመወሰን ስልጣን የሚፃረር ህገ ወጥ ደብዳቤ መላኩን ኣስመልክቶ ዛሬ በፓርቲው ዋናው ፅህፈት ቤት -መቐለ መግለጫ ሰጥቷል።
፩) የትግራይ ክልል እንጂ የአማራ ክልል የግዛት ጥያቄ ብሎ ነገር እንደሌለ፣ አማራ ክልል የሚባል በታሪክ የሌለና ኢህአደግ ሰራሽ ክልል እንደሆነ፣ ትግራይ ግን ከጥንት ከጥዋቱ ጀምሮ የነበረ ክልል እንደሆነ፣ የትግራይ ዳር ድንበር ከአልውሃ እስከ ለማሊሞ እንደሆነ ግልፅ አድርጓል።
-ባይቶና የዓባይ ትግራይ ሉኣላዊ ግዛቶች (አልውሃና ሊማሊሞ ጨምሮ) ለመመለስ ኣበክሮ እንደሚታገልም በመግለጫው አሳውቋል።
፪) የፌዴሬሽን ምክርቤት የላከው ደብዳቤ ሌላው የጦርነት ነጋሪት እንደሆነ፣ የፌዴሬሽን ምክርቤት ሳይሰበሰብ በብልፅግና ግለሰዎች ትእዛዝ ለአፈጉባኤው በማዘዝ የተፃፈ የሽብር ደብዳቤ እንደሆነ ባይቶና ገልፀዋል።
-ባይቶና የትግራይ ምርጫ የሚያደናቅፍ ማንኛውም እርምጃ ለማክሸፍ ዝግጁ እንደሆነ
-ይህ ምርጫ እንከን ይኑረው ኣይኑረው የሚመለከተው የትግራይ ህዝብና የትግራይ ብሄርተኛ ድርጅቶች ብቻ እንጂ ህገወጡ ብልፅግናና በሱ ሳንባ የሚተነፍሱ የአሃዳዊ ስርኣት ቅሪቶች እንዳልሆነ፣
- ምርጫው ታሪካዊና የሪፈረንደም አንድምታ ያለው ስለሆነ በምንም ተአምር የማይታለፍ መሆኑና የትግራይ ሉዓላዊነትና ደህንነት ለመጠበቅ ባይቶና ሁሉም ዓይነት መስዋእት ለመክፈል ግምባር ቀደም ሆኖ ለመታገል ቁርጠኛና ፅኑ አቋም መያዙ በዛሬው መግለጫው አንፀባርቋል።
ድል ለትግራይ ሰማእታት!
ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ( ባይቶና)
ሓምለ 28/11/2012 ዓ/ም
መቐለ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ