Ads Here

ማክሰኞ 4 ኦገስት 2020

በአብዬ አዲሱ የሀይል አዛዥ ሆነው የተሾሙት ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ አቀባበል ተደረገላቸው!



በሱዳን አብዬ ለተሰማራው በተባበሩት መንግስታት ጊዜያዊ የሰላም አስከባሪ / ዩኒስፋ የሀይል አዛዥ በመሆን የተሾሙት ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በአብዬ ዋና ማዘዣ ሲደርሱ በተለዋጩ የሀይል አዛዥ ሜ/ጄ መሀሪ ዘውዴና በከፍተኛ የዩኒስፋ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ግዳጁ ከተጀመረ ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ ስምንተኛው ኢትዮጵያዊ የሀይል አዛዥ በመሆን የተሾሙት ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በተለያዩ የአመራር ሀላፊነቶች ላይ  ከ30 ዓመታት በላይ አገልግለዋል፡፡በ2007 በሶማሊያ የአሚሶም የሴክተር አዛዥ በመሆንም ግዳጃቸውን ፈፅመዋል፡፡

ሜ/ጄ ከፍያለው የመጀመሪያ ዲግሪ ከሩሲያ ጥምር ጦር አካዳሚ በወታደራዊ ሳይንስ፣ የማስትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ በአሜሪካው ሀሽላንድ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል፡፡ ጄኔራል መኮንኑ ከሀገር ውስጥ ቋንቋ በተጨማሪ ሩሲያኛና እንግሊዘኛ ቋንቋ ይናገራሉ፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ