Ads Here

ማክሰኞ 4 ኦገስት 2020

ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ





ባለፉት አሥራ አንድ ቀናት ከ 46 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
 ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከሐምሌ 16 እስከ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ከሀገር ለማስወጣት እና ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መሆኑ ተገልጿል።
 
ከተያዙት ዕቃዎች መካከል ስማርት ስልኮች ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት፣ ሲጋራ፣ መድኃኒት፣የብር ጌጣጌጥ፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ ልባሽ ጨርቆች ይገኙበታል ተብሏል።
 
ከዚህ በተጨማሪም ግምታዊ ዋጋ ያልወጣላቸው በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገቡ ተሽከርካሪዎች እና ከሀገር ሊወጣ የነበረ ቡና መያዙን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ