የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2012 በጀት ዓመት ለሱዳንና ጅቡቲ ካቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ66 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ቢሮው በ2012 በጀት ዓመት 56 ነጥብ 92 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ከ66 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰብስቧል፡፡
ይህም የዕቅዱን 116 ነጥብ 5 በመቶ በማከናወን ከዕቅድ በላይ ገቢ መገኘቱ ተገልጿል፡፡ በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው ገቢ 37 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ከጅቡቲ እና ቀሪው 29 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከሱዳን የተገኘ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ ዓመት ከሁለቱ ሀገራት የተገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ገቢ ከ2011 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተነግሯል፡፡ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች በቂ ውኃ መያዛቸውና የኃይል መቆራረጥ መቀነሱ ለዕቅዱ መሳካት አስተዋጾ ማድረጉ ተብራርቷል፡፡
በቅርቡም ለኬኒያ የኤሌክቲክ ኃይል በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እና የኤሌክትሪክ ኮንቨርተር ጣቢያ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያ ከሦስቱ ሀጋራት በተጨማሪ በቀጣይ ከሶማሌ ላንድ፣ ከታንዛኒያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለመፍጠር የሁለትዮሽ ግንኙነት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ