Ads Here

ማክሰኞ 4 ኦገስት 2020

በአዲስ አበባ የተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የአውሮፕላን በረራዎችን አስተጓጎለ


በዛሬው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ሳቢያ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ሊያርፉ የነበሩ አውሮፕላኖች በሌሎች የአውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ ተደረገ።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፥ አብዛኛው የከተማዋ ክፍልም በጉም ተሸፍኖ ነው የዋለው።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የአውሮፕላን በረራዎችን በማስተጓጎል ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መረጃም፥ “ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ አውሮፕላኖቻችን በአቅራቢያ ወደሚገኙ የአየር ማረፊያዎች ተመልሰው እንዲያርፉ ተደርጓል” ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚሕ ምክንያት ለተከሰተው መጉላላት ይቅርታ በመጠየቅም፤ ሁኔታውን እየተከታተለ ተጨማሪ መረጃ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ