Ads Here

እሑድ 9 ኦገስት 2020

የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር በፍጥነት ምርጫ እንዲደረግ መስማማታቸው ተገለጸ

የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዳይብ መንግስታቸው በገጠመው ተቃውሞ ምክንያት በቅርቡ ምርጫ እንዲደረግ መስማማታቸውን ትናንት ምሽት ላይ በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው ገልጸዋል፡፡

መንግስታቸው በቅርቡ ምርጫ እንደሚያደርግ ገልጸው ለሁለት ወራት ብቻ እርሳቸው እንደሚመሩ ተናግረዋል፡፡ 

በቤሩት ደረሶ የነበረውን ፍንዳታ ተከትሎ በርካቶች ከፈረንጆቹ ነሐሴ 6 ቀን ጀምሮ ጎዳና በመውጣት ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፈኞቹ የውጭ ጉዳይ፣የአካባቢ እና የኢኮኖሚ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አካባቢዎችን ማጥለቅለቃቸው ነው የተሰማው፡፡

ይህንን ተከትሎ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርብ ምርጫ ይደረጋል ማለታቸው የተሰማው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤሩት ወደብ የደረሰው ከፍተኛ ፍንዳታ የሙስና እና የአስተዳደር ብልሽት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እርሳው የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ላይ እስኪስማሙ ድረስ ለሁለት ወራት ሀገሪቱን እንደሚመሩም ተገልጿል፡፡ 


እንደ አል አረቢያ ዘገባ እስካሁን በፍንዳታው 158 ሰዎች ሲሞቱ ከ5ሺ በላይ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ