በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ7 ሺህ 358 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 469 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 17 ሺህ 999 የደረሰ ሲሆን÷ በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው 10 ሺህ 518 ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
በአሁኑ ወቅት 68 ሰዎች በፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገኙ ሲሆን÷ 245 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።
ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙት ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 195 እንደደረሰም ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።
እንዲሁም በ24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ ምክንያት 284 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በአጠቃላይ ለ429 ሺህ 712 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ