በሶማሊያ በጎርፍ ምክንያት ቁጥራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
በድርጅቱ የሰብአዊ መብት አስተባባሪ ቢሮ እንስታወቀው በወቅታዊ ዝናብ የሚከሰቱ ድንገተኛ ጎርፎች ምክንየት 191800 ሰዎች በግንቦትና በነሃሴ ወራት ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ እንደቢሮው ከሆነ ነዋሪዎች ከባለፈው ሰኔ ጀምሮ መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡ በአብዛኛው የደቡባዊና የማእከላዊ ሶማሊያ ከባለፈው አመት የከበደ ዝናብ እየዘነበ እንደሆነም ቢሮው አመልክቷል፡፡
በሂርሻበሌ፣በደቡብ ምእራብና በጁባላንድ ግዛቶች የሚገኙ ነዋሪዎች በጎርፍ ተጠቅተዋል፡፡
የዋቢሸበሌ ወንዝ ከፍታ በሚቀጥሉት ሳምንታት ይጨምራል የሚል ግምት አለ፤ የጎርፍ አደጋም ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በሶማሊያ ወደ 150ሺ ሄክታር የሚጠጋ በባልካድ፣ ጆውሃርና በማሃዳይ ቀበሌዎች የሚገኝ የእርሻ መሬት በጎርፍ ማጥለቅለቁን ተነግሯል፡፡ በባንዲር ግዛት የተፈናቀሉ አራት ሰዎች መሞታቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ መጠለያ ማጣታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ድርጅት አስታውቋል፡፡
በሀገሪቱ የተከሰተው ኮሮናና የአንበጣ ወረርሽኝ በጤና ስርአቱ ላይ ከባድ ጫና ማሳደሩ ተነግሯል፡፡ ባለፈው ሀምሌ ወር መንግስት በታችኛውና በመካከለኛው የዋቢ ሸበሌ ወንዝ ተፋሰስ በደረሰው ጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው የእርዳታ ድርጅቶችን ድጋፍ ጠይቆ ነበር፡፡
በጎርፍ ምክንያት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡የድርጅቱ የሰብአዊ መብት አስተባባሪ ቢሮ እንደገለጸው በጎርፍ አደጋ ምላሽ የመስጠት አቅሙ በሶስት እጥፍ ቢጨምርም፤አሁንም የምግብ፣የመጠለያና ምግብ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ክፍተት መኖሩን አስታውቋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ