የኮሚሽኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢኒስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት የጭነት አይሱዙ ተሸከርካሪ ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ከመልካበሎ ወረዳ በሬዳ ሸቀጣ ሸቀጦችን ጭኖ እና 21 ሰዎች አሳፍሮወደ ሐረዋጫ ከተማ ሲጓዝ ሙሊሳ ሃቃ ቀበሌ ተገልብጦ አደጋው ደርሷል፡፡
በዚህም የ13 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው ሾፌር ለጊዜው ከአካባቢው መሰወሩንና ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑም ታውቋል፡፡
በአካባቢው የመንገድ ችግር በመኖሩና የህዝብ ተሸርካሪዎች በአካባቢው ባለመገኘታቸው ህብረተሰቡ በጭነት መኪና ለመጓጓዝ እንደሚገደድና በተለያዩ አካባቢዎችም ከዚህ በፊት ተመሳሳይ አደጋ ይደርስ እንደነበርም ኢኒስፔክተሩ አስታውሰዋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ