Ads Here

ዓርብ 7 ኦገስት 2020

በጥቁር አንበሳ የህክምና ቤተ ሙከራ ህይወቷ አልፎ የተገኘችው ሃይማኖት በዳዳ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 7 የጥበቃ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

 

በጥቁር አንበሳ የህክምና ክፍል ቤተ ሙከራ ውስጥ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ህይወቷ አልፎ የተገኘችው ሃይማኖት በዳዳ ግድያ ጋር በተያዘ የተጠረጠሩ 7 የጥበቃ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በእነ ሃብቴ ጓቤ መዝገብ የቀረቡት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ መርማሪ ፖሊስ እየሰራ ያለውን ስራ አስመልክቶ ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀ ሲሆን ግድያ ፈጽሜያለሁ በሚል የእምነት ክህደት ቃሉን ከሰጠው ደግነት ወርቁ በተጨማሪም እነዚህ ተጠርጣሪዎች ከግድያው ጀርባ ያላቸው ግንኙነት እየለየ መሆኑን ፖሊስ አስረድቷል፡፡

ሟች ተማሪ በአማካሪዋ ተደውሎላት ወደ ጥቁር አንበሳ የሄደች ሲሆን የስልክ ልውውጡን ፖሊስ እየመረመረ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ሁለተኛ ተጠርጣሪ በወቅቱ የኤጀንሲ ጠባቂዎች መሆናቸውን በመጥቀስ ተማሪ ሃይማኖት ህይወቷ አልፎ የተገኘበት ህንፃ በበጀት ጉድለት ምክንያት ጠባቂ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

የዋስትና መብታችን ይጠበቅ ያሉ ጠይቀዋል ፍርድ ቤት በበኩሉ መርማሪ ፖሊስ የተናጠል ተሳትፏቸውን እንዲያቀርብ በማዘዝ የ7 ቀን ጊዜ ፈቅዷል፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ