Ads Here

ሐሙስ 6 ኦገስት 2020

ከትናንት በስትያ ምሽት በቤሩት በደረሰው ፍንዳታ እስካሁን 10 ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉ ተነገረ።

ከትናንት በስትያ ምሽት በቤሩት በደረሰው ፍንዳታ እስካሁን 10 ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉ ተነገረ። 

በቤይሩት ነዋሪ የሆነችዉ ኢትዮጵያዊትዋ ትዕግስት ለዶቼ ቬለ በስልክ እንዳረጋገጠችዉ የአገሪቱ መንግሥት እስካሁን አስር ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉን አረጋግጦአል።

በቤይሩት ነዋሪ የሆነችዉ ይህች ኢትዮጵያዊት መዲና ቤይሩት አሁንም በፍርስራሽ ስር የተቀበሩ አስክሪንን እያወጣች መሆኑን ተናግራለች።

 በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል ተመስገን ዑመር ትናንት ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት በሊባኖስ ከ 250 እስከ 300 ሺህ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ፤ አብዛኞቹ ደግሞ ደግሞ የሚገኙት ቤይሩት ከተማ ዉስጥ ነዉ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ