በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ጦር (አሚሶም) ጥላ ስር በሶማሊያ ኪስማዮ ተሰማርቶ የነበረው የኢትዮጵያ ሻለቃ ጦር ግዳጁን አጠናቆ ወጣ፡፡
በሴክተር ስድስት የነበረው 4ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃው ግዳጁን አጠናቆ በድል መመለሱንም የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡
ሞተራይዝድ ሻለቃው በሶማሊያ በነበረው ቆይታ ለሀገሪቱ ሰላም መስፈንና የኢትዮጵያን የሰላም አምባሳደርነት ዳግም ማሸመሰክር ችሏል፡፡
የአስረካቢው ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል መንገሻ ሞላ ባደርጉት ንግግር ፣ ሻለቃው በሶማሊያ በነበረው ቆይታ የቀጠናውን ሰላም ማረጋገጥ፣ሰራዊቱንና ህዝቡን ማቀራርብ እና ከመንግስት መዋቅሩ ጋር በቅንጅት በመስራት ስኬታማ ግዜያትን ማሳለፍ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
የተረካቢው ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ገ/መድህን ገ/መሰቀል በበኩላቸው፣አስረካቢው ሻለቃ በነበረው የግዳጅ ቆይታ የፈፀማቸውን ገድሎች አድንቀው፣ተረካቢው ሻለቃም ከዚህ በበለጠ ግዳጁን ለመውጣት ጠንክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ