ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ክስ አቋረጠ
(ኢፕድ)
የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ አደረገ፡
የኮረና ቫይረስ ማህበራዊና ሰብአዊ ቀውስ ከማስከተሉ በተጨማሪ ከባድ የኢኮኖሚ ችግር እያስከተለ ሲሆን በኢኮኖሚው መዳከም ምክንያት ግብር ከፋዬችና በአጠቃላይ የንግድ ማህበረሰቡ ስራቸውን ለማቆም ስለሚገደዱ ፣ በርካታ ዜጎች ከስራ ስለሚያፈናቅሉ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር የሚዳርግ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ያለባቸውን ውዝፍ የግብር፣ የታክስ እና ቀረጥ ነፃ በማቃለል ለታክስ ክፍያ ሊያውሉት ይገባ የነበረውን ገንዘብ ለስራ ማስኬጃ በማዋል በንግድ ስራ ውስጥ እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንዲችሉ መንግስት የታክስ ምህረት ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም መንግስት የኢኮኖሚ ጫናውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ኪሳራን ከማሸጋገር ጀምሮ የተለያዩ ተጨማሪ ውሳኔዎችን ወስኗል፡፡
በዚሁ መሰረት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግም በመንግስት የተሰጡትን የተለያዩ ውሳኔዎችን መነሻ በማድረግ የወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ ዝርዝር የውሳኔ መመሪያ ( exit strategy ) በማዘጋጀት ነጋዴውን የሚመለከቱ የወንጀል የምርመራ መዛግብቶች እና በፍርድ ቤት በመደበኛና በይግባኝ በክርክር ላይ የሚገኙ ያለደረሰኝ ግብይት፣ ታክስ ስወራ እና አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ክስ እንዲሁም በኮንትሮባንድ ወንጀል በምርመራ ላይ ያሉና ክስ የተመሰረተባቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ክሳቸው እንድቋረጥ ተደረጓል፡፡
ሰለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘ በቀጣይ የሚቋረጡ መዛግብቶች እንዳሉ ሆኖ በመመሪያው መሰረት እስካሁን የተቋረጡ መዛግብት ዝርዝር ከዚህ በታች ባለው ምስል ማግኘት ይቻላል ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ