የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካ ብሄራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር /አኖካ/ ለኦሎምፒክ ስፖርት ዕድገት ድጋፍ ላደረጉ መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።
ለኢትዮጵያ ስፖርት እና ለኦሎምፒክ ንቅናቄ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ይህ በአፍሪካ በስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የሆነው ሽልማት ተሸላሚ መሆናቸውን አኖካ አስታውቋል።
ማህበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በቀጣይ በሚመረጥ ቦታና ጊዜ ሽልማቱ እንደሚበረከትላቸው አስታውቋል።
ዘንድሮ ሊካሄድ የነበረውን የቶክዮ ኦሎምፒክን መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ ቀደም ብላ ባሉት ወራት ሰፊ ከማስ ስፖርት ጋር በማስተሳሰር ሀገር አቀፍ የኦሎምፒክ ስፖርት ንቅናቄ ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ