በትግራይ ክልል ለሚደረገው ስድስተኛው ክልላዊ ምርጫ የሚሳተፉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ከነሃሴ 5/2012 ዓ/ም ጀምሮ አጠቃላይ የምርጫ ቅስቀሳ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
በመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም፣ በበጀት ድልድል እና በሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በተፎካካሪ ፓርቲዎችና በምርጫ ኮሚሽን አመራሮች መካከል ለሁለት ቀን ውይይት ሲደረግ ቆይቶ ትላንት መጠናቀቁን ከትግራት ቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ስምምነት በማድረግ የምርጫው ጊዜ ገደብ ተላይቶ በቀጣይ የውይይት መድረክ ይፋ እንደሚደረግ ገልጿል።
በትግራይ ክልል በሚደረገው ምርጫ 5 ተፎካካሪ ፓርቲዎች (ህወሓት፣ ባየቶና ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ ፣ አሲምባ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት) እና 11 የግል እጩዎች ተወዳዳሪዎች መመዝገባቸው ይታወሳል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ