Ads Here

ሰኞ 3 ኦገስት 2020

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት አመቱ ከ47 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ



ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት አመት 47 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱ ተገለጸ። የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በሰጡት መግለጫ ÷ ገቢው ከእቅዱ 105 ነጥ ብ 1 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል።

ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ31 ነጥብ 4 በመቶ ብልጫ መኖሩን ጠቁመው ÷ ተቋሙ ከውጭ የስልክ ጥሪ 147 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱን ገልጸዋል።

ከዚያም ባለፈ 10 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብድር መመለስ ተችሏልም ነው ያሉት።

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥርም ከባለፈው አመት በ5 ነጥብ 8 በመቶ አድጎ 46 ነጥብ 2 ሚሊየን መድረሱንም አንስተዋል።


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ