በሶማሊያ ለተከሰተው ፍንዳታ አልሸባብ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ገልጿል
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሹ በስቴዲየም አካባቢ በተከሰተ ከባድ ፍንዳታ በትንሹ 8 ሰዎች መሞታቸውንና 14 ሰዎች መቁሰላቸውን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተናግረዋል፤ ለጥቃቱም አልሸባብ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡
ፍንጻታው ከተከሰተ በኋላ ወታደሮች ተኩስ መክፈታቸውን ሃሊማ አብዲሳላም የተባሉ የሶስት ልጆች እናት ሴት ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
“ወደ ቤት ሮጠናል፤ ወዲያውኑ መኪና በደም የተሸፈኑ ወታደሮችን ጭኖ በፍጥነት ሲያልፍ ማየት ችያለሁ” በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል፡፡ የጦር ኃላፊ የሆነው ሜጄር አብዱላሂ ሞሃሙድ ድርጊቱ ጥቃት መሆኑን ገልጿል፡፡“የአጥፍቶ ጠፊ ቦንብ መሆን አለበት፤ እኔ አሁን ቁስለኞችን እየወሰድኩ ነው” ብሏል፡፡
ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስጃለሁ ያለው የአልሸባብ ቡድን ወታደራዊ ስምሪት ቃል አቀባይ የሆነው አብዲያሲስ አቡ ሙሳብ እንደገለጸው ዋነኛ ከሃዲ በሆነው ወታደራዊ ካምፕ ላይ ስኬታም የመስዋእትንት ስምሪት መካሄዱን አስታውቋል፡፡
ቃል አቀባዩ ብዙ ጠላቶቻችን ሞተዋል፤ ቆስለዋል፤ ወታደራዊ መኪኖችም ወድመዋል ብሏል፡፡
በፈረንጆቹ 1991 የጎሳ መሪዎች የሀገሪቱን መሪ ሲያድ ባሬን ከስልጣን አስወግደው ወደ እርስበእርስ ግጭት ከገቡ በኋላ ሶማሊያ በብጥብጥ ውስጥ እየዳከረች ትገኛለች፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ